Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ በ173 ሚሊየን ብር ያስገነባውን ኔትወርክ ማስፋፊያ አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከተማ በ173 ሚሊየን ብር ያስገነባውን የአራተኛ ትውልድ (4 ጂ) ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ ኔትወርክ ማስፋፊያን አስመረቀ።

ማስፋፈፊያው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማጠናከር እየተደረገ ላለው እንቅስቃሴ አስተዋጽኦ እንዳለው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይዎት ታምሩ ተናግረዋል።

ማስፋፊያው እየጨመረ ላለው የተጠቃሚዎች ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት ያለመ መሆኑንም አስረድተዋል።

በቀጣይም ከፍተኛ የኢንተርኔት ፍላጎት ያላቸውን ከተሞች በመለየት ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ 4 ጂ ተግባራዊ ይደረጋልም ብለዋል።

ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ አገልግሎቱ በአዲስ አበባ ከተማ የሞባይል ኢንተርኔት አጠቃቀም ከፍተኛ በሆነባቸው ቦታዎች የሚተገበር ነው ተብሏል።

የኔትወርክ ማስፋፊያ ግንባታው በቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ የተከናወነ ሲሆን፥ ሙሉ ወጪው በመንግስት የተሸፈነ ነው።

በይስማው አደራው

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.