የሀገር ውስጥ ዜና

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ጥሩ ለፈጸሙ ሠራተኞቹ ዕውቅና ሰጠ

By Tibebu Kebede

September 05, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ውስጥ መልካም አፈፃፀም ላሳዩ ሠራተኞቹ ዕውቅና ሰጠ።

የሣይስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የአስተዳደር ቢዝነስና የአይሲቲ ፎረም ዛሬ ተጠናቋል።

የ2013 ትምህርት ዘመን በኮቪድና በተለያዩ የፀጥታ መደፍረሶች የታጀበ እንደነበር የገለፁት የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዑባህ አደም፣ በእነዚህ መሠናከሎች ላልተበገሩት የዩኒቨርስቲው መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተለይም በኮቪድ 19 ባክኖ የነበረውን የ2012 ትምህርት ዘመን ለማካካስ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት፣ ተደራራቢ ኮርሶችን ሲሰጡ የነበሩ መምህራን ከስራ ሃላፊነታቸውም በላይ የዜግነት ግዴታቸውን ተወጥተዋል ብለዋል።

በመድረኩ በተመራቂ የአርክቴክቸር ተማሪዎች የተሠራ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ዑባህ አደም ፎቶ ለጨረታ ቀርቦ በ22 ሺ ብር ተሸጧል። ከጨረታው የተገኘው ገንዘብም ለበጎ አድራጎት ስራ እንደሚውል ተገልጿል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!