የሀገር ውስጥ ዜና

የመስከረም ወር የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

By Feven Bishaw

September 06, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስከረም ወር የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም ከጳጉሜን 1 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ.ም የሁሉም ነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነሐሴ ወር በነበረበት እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡