Fana: At a Speed of Life!

የ60 ዓመት አዛውንት የምትመስለው የ15 ዓመቷ ታዳጊ …

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ60 ዓመት አዛውንት የምትመስለው የ15 ዓመቷ ልጃገረድ ወጣት ለመምሰል ቀዶ ጥገና (ፕላስቲክ ሴሪጀሪ) ማድረጓ ተነግሯል።

ሺዮፌንግ የተባለቸው የ15 ዓመት ቻይናዊት ቀዶ ጥገና ህክምና ያደረገችውም ጓደኞቿ እና የአካባቢው ማህበረሰቡ በሚያደርስባት መገለል ምክንያት መሆኑን ተናግራለች።

በተወሰኑ ሰዎች ላይ በሚከሰተው የቆዳ በሽታ የተጠቃችው ሺዮፌንግ በሰዎች በእሷ ላይ በሚያሳዩት የተዛባ አመለካከት ምክንያት ትምህርቷን እስከማቋጥ ደርሳ ነበር።

ሁኔታውን መቆጣጠር ያቃተት ሺዮፌንግ በማህበረሰቡ የሚደርስባትን መገለል ለመቋቋም የነበራትን የአዛውንት የሰውነት ገጽታ በቀዶ ጥገና ማስተካከል መቻሏ ተሰቷምል።

72 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወጪ የተደረገበት ይህ ቀዶ ጥገናም ሺዮፌንግ የእድሜ እኩዮቿን የሚመስል ተክለ ሰውነት እንድትጎናጸፍ አስችሏታል።

በሁኔታው እጅግ መደሰቷን የገለጸችው ታካሚዋ፥ በደረሰባት መድልዎ ምክያንት ያቋረጠቸውን ትምህርት የምትቀጥል መሆኑን ገልጻለች።

ትምህርቷን ስትጨርስም ዶክተር በመሆን በመሰል ችግር ለሚሰቃዩ ወገኖች እገዛ የማድረግ ፍላጎት እንዳላት ተናግራለች።

ምንጭ፦ኦዲቲ ሴንትራል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.