በማይጠብሪ ግንባር ከተለያዩ አካባቢዎች የሚቀርበው ድጋፍ ቀጥሏል
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በጎንደር ከተማ የሚኖሩ ባለሀብቶች፣ ነጋዴዎችና የሲቪክ ማህበራት ማይጠብሪ ግንባር ለተሰለፈው ሠራዊት ግንባር ድረስ በመገኘት የተለያዩ ድጋፎችን አድርገዋል።
የድጋፉ አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን ሲሳይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ የተሰጠው ድጋፍ 11 ሺህ አልባሳት ፣ ምግብ፣ 4 ኩንታል ቴምር፣ 600 ካርቶን ብስኩትና 500 ደርዘን ውሃ ሲሆን÷ ወደፊትም ድጋፉ ይቀጥላል ብለዋል።
በተመሳሳይ የሜጫ-መርዓዊ በጎ አድራጎትና ልማት ማህበር በውጭ ሀገር የሚኖሩ ወገኖችን አስተባብረው 50 በግና ፍየል፣ 300 ኪሎ ማር፣ 5 ኩንታል ስኳር፣ 80 ካርቶን ደረቅ ምግብና 1 ሺህ አልባሳት በግንባር ለተሰለፉ ዘማቾች ቦታው ድረስ ተገኝተው አበርክተዋል።
በተጨማሪም ደጀን ለኢትዮጵያ የተባለው የበጎ አድራጎት ማህበር 3ተኛ ዙር ድጋፍ በደባርቅ ግንባር የሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊት ለማበረታታት የምሳ ግብዣ አድርጓል።
በዚህም ከ2 ሺህ በላይ ለሆኑ የሰራዊቱ አባላት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን÷ ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ብርጌድ ለሚገኙ ሴት የሰራዊቱ አባላት የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ አድርጓል።
እስካሁን ድረስም ከ750 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ በተለያዩ ግንባሮች ለሚገኘው የወገን ጦር ድጋፍ እንዳደረገ አስተባባሪዎቹ ገልፀዋል።
በሙሉጌታ ደሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!