የሀገር ውስጥ ዜና

በጉጂ ዞን 2 ሺህ 858 የክላሽ እና ብሬን ጥይቶች ተያዙ

By Alemayehu Geremew

September 06, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉጂ ዞን፣ ጎሮ ዶላ ወረዳ፣ ቢታታ ቀበሌ ሠላም ለማደፍረስ ተግባር ሊውሉ የነበሩ 2 ሺህ 858 የክላሽ እና ብሬን ጥይቶች ተይዘዋል፡፡

ለዕኩይ ዓላማ ሊውሉ የነበሩት ተተኳሽ ጥይቶች፣ ታርጋ ቁጥሩ 35819A.A በሆነ የአይሱዙ መኪና ተጭነው፥ መኪናው ወደ ኔጌሌ ሊያመራ ሲል በፀጥታ አካላት መያዛቸውን የጉጂ ዞን አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወልዴ ዱጎ ገልፀዋል፡፡

ከተተኳሽ ጥይቶቹ በተጨማሪም 32 የጦር ሜዳ ልብሶች መያዛቸውንም ኦቢኤን ዘግቧል፡፡