የሀገር ውስጥ ዜና

የትምህርት ሚኒስቴር የኮቪድ19 ፕሮቶኮል አዘጋጀ

By Feven Bishaw

September 06, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት አሰጣጡ እንዴት መሆን እንዳለበት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኮቪድ19 ፕሮቶኮል አዘጋጅቷል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በ2013ዓ.ም የትምህርት ዘመን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባስቀመጠው የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል መሰረት ትምህርት በቀንና ፈረቃ ሲሰጥ መቆየቱ ተገልጿል፡፡