Fana: At a Speed of Life!

የህልውና ዘመቻውን ለሚቀላቀሉ የተቋሙ ሠራተኞች ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገራችን እየተካሄደ የሚገኘውን የህልውና ዘመቻ ለሚቀላቀሉ ሁለተኛ ዙር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች ሽኝት ተደረገ፡፡

በአሸባሪው የህወሓት ጁንታ ቡድን እየተሰነዘረ ያለውን ሀገር የማፍረስ አደጋ ለመቀልበስ ተቋሙን ወክለው ለሚዘምቱ ሠራተኞች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የዋና ሥራ አስፈጻሚ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙላት ገዛኸኝ በበኩላቸው÷ ጀግኖች አባቶቻችን ከውጭ ወራሪ ጠብቀው ያቆዩዋትን ሀገር በመካድ ጥቃት እያደረሰ የሚገኘውን የህወሓት ከሃዲ ቡድን ለመደምሰስ ተቋሙ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

ሰራተኞቹ በተቋሙ የነበራቸውን ተሳትፎ በህልውና ዘመቻው በመድገም ተቋማቸውን እና ሀገራቸውን እንደሚያኮሩ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

ሽኝት የተደረገላቸው ሠራተኞች አሸባሪውን ቡድን ለመከላከልና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት በሚደረገው ዘመቻ ለመሳተፍ ያነሱት ጥያቄ በተቋሙ ተቀባይነት አግኝቶ በክብር ሽኝት መደረጉ እንዳስደሰታቸው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

ዘማቾቹ ሀገር ከሁሉም በላይ መሆኗን በማንሳት ሥራም ሆነ ህይወት ሊቀጥሉ የሚችሉት ሀገር ሲኖርና ሰላም ሲሆን ብቻ ነው ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.