Fana: At a Speed of Life!

በየደረጃው ያለው የአገልጋይነት ስሜት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መሄድ አለበት-ወ/ሮ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ማገልገል ከምንም በላይ ክቡር የሆነ ተግባር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአገልጋይነት ክብር ቀንን በማስመልከት ከፅዳት ሰራተኞች እና ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን የፅዳት ዘመቻ አካሄደዋል።

በመርሃ ግብሩ ምክትል ከንቲባዋ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ማገልገል ከምንም በላይ ክቡር የሆነ ተግባር መሆኑን አውስተዋል፡፡

አገልግሎት ሁሉ ሰው እድሜውን ሁሉ እየሰጠ እና እየተቀበለ የሚኖበት የህይወት አካል ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ÷ በየደረጃው ያለው የአገልጋይነት ስሜት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መሄድ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

አገልጋይነት በእውነት ለገባው ትንሽ ትልቅ የማይባል፤ ከደሳሳ ቤት ጀምሮ እስከ ቤተ መንግስት አስቀድሞ ያለ የነበረ ፤ ወደፊትም የሚኖር ታላቅ ተግባር ሲሆን መርሁም ታማኝነት፣ ቅንነት እና አክብሮት መሆኑንም ምክትል ከንቲባዋ ገልፀዋል።

በማዘጋጃ ቤት ቅጥር ጊቢ በተካሄደው የጽዳት ዘመቻ መርሃ ግብር የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት፣የጽዳት ሰራተኞች ፣የእሳት አደጋ መከላከል ባለሙያዎች፣ ወጣት በጎ ፈቃደኞች እና የመንግስት ሰራተኞች መሳተፋቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የአገልጋይነት ክብር ቀንን አስመልከቶ በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የፅዳት ዘመቻ መርሃ ግብር በመከናወን ላይ ይገኛል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.