የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ደሴ ለሚገኙ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ2ነጥብ 5ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

September 07, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ደሴ ለሚገኙ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ2ነጥብ 5ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ድጋፍ አድርጓል።

በድጋፉም 100 ኩንታል ስንዴ፣ 350ኩንታል በቆሎ፣ 800ብርድ ልብስና 20 ማዳበሪያ ቦንዳ የተለያዩ አልባሳት ለተፈናቃዮቹ ተሰጥቷል።

የተቋሙ ተወካይ አቶ አቤል አዳሙ ለደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ቁሳቁሱን አስረክበዋል።

ድጋፉ ከደሴ በተጨማሪ ለአፋርና ለጎንደር ተፈናቃዮችም የተደረገ ሲሆን÷የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በጥቅሉ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ አድርጓል።

በስንታየሁ መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!