የተመራቂ ተማሪዎችና ቀጣሪ ድርጅቶች የስራ አውደ ርዕይና ፎረም ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ከ15 ሺህ በላይ ተመራቂ ተማሪዎች እና ከ300 የሚበልጡ ቀጣሪ ድርጅቶች የሚሳተፉበት የስራ አውደ ርዕይና ፎረም ተጀመረ።
አውደ ርዕዩንና ፎረሙን ያዘጋጁት ደረጃ ዶት ኮም ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ፣ ከስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽንና ሌሎችም ተቋማት ጋር በመተባበር ነው።
በፎረሙ ላይ የደረጃ ዶት ኮም ፕሮግራም ማናጀር ሲሀም አየለ እንዳስታወቁት እስከ መስከረም 6/2014 ዓ.ም. በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሚቆየው በዚሁ ዝግጅት ከ15 ሺህ በላይ ተመራቂ ተማሪዎች እና ከ300 የሚበልጡ ቀጣሪ ድርጅቶችን ለማሳተፍ ታቅዷል።
ዓላማ ውም የተለያዩ ቀጣሪ ድርጅቶች ብቁ የሆነ የሰው ሃይል የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት መሆኑን አስረድተዋል።
የኢንተርኔት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንንቀጣሪ ድርጅቶችንና ባለድርሻ አካላትን በአንድ መድረክ ለማገናኘት እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ይህም ምሩቃን ያለምንም ውጣ ወረድ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በሥራ እድል ዙሪያ በማገናኘት ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
በተለይ ምሩቃንን በሥራ ዓለም ተፈላጊ በሆኑ ክህሎት በማሰልጠን የወጣቶችን ስራ አጥነት ችግር ለመቀነስ ከዩኒቨርስቲዎች ጋር በቅርበት እየሰራ ነው ብለዋል።
እስካሁን ባደረጉት እንቅሰቃሴ ከ100 ሺህ በላይ ተመራቂ ተማሪዎችን ሲያሰለጥኑ 50 ሺሀ የሚሆኑትን የስራ እድል እንዲያገኙ ማመቻቸታቸውን ጠቁመዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share