የሀገር ውስጥ ዜና

አካል ጉዳተኞች ተገቢውን የፍርድ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል አሰራር ተዘርግቷል

By Meseret Demissu

September 07, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  አካል ጉዳተኞች በፍድ ቤቶች የተሻለና ተገቢ የሆነ አገልግሎት እንዲያገኙ የአሰራር ሥርዓት መዘርጋቱን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ማዓዛ አሸናፊ ገለጹ።

የኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኛ ሴቶች ብሔራዊ ማኅበር 20ኛ ዓመቱን ዛሬ አክብሯል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት መዓዛ አሸናፊ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፤ አካል ጉዳተኞች ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው እንዲከበር በፈርድ ቤቶች በኩል እየተሰራ ነው።

በፍርድ ቤቶች በሚካሄዱት የአሰራር ማሻሻያ ሥራዎች አካል ጉዳተኞች ከዚህ ቀደም ከነበረው የተሻሉ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠረላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በቅርቡ በጸደቀው የፌደራል ፍርድ ቤቶችን አዋጅ ቁጥር 1234 ውስጥ አካል ጉዳተኞችን የተመለከቱ  አንቀጾች መካተታቸውን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኛ ሴቶች ብሔራዊ ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ድባቤ ባጫ አካል ጉዳተኞች መብታቸው ለማስከበር ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።

ያም ሆኖ ማኅበሩ የመሥሪያ ቦታ አለመኖሩን ጠቁመው የሚመለከተው አካል ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ለማኅበሩ የመስሪያ ቦታ ለመስጠት ጥረት ይደረጋል ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን