የሀገር ውስጥ ዜና

“መቶ ለወገኔ” የተሰኘው የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በጋምቤላ ክልል በይፋ ተጀመረ

By Feven Bishaw

September 08, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና በህወሓት የሽብር ቡድን ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል “መቶ ለወገኔ” የተሰኘ ንቅናቄ በጋምቤላ ክልል በይፋ ተጀምሯል፡፡

የጋምቤላ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሯች ጎች “መቶ ለወገኔ” የድጋፍ ንቅናቄ በተለይ ወጣቶች የሚሳተፉበት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡