የሀገር ውስጥ ዜና

ትምህርት ሚኒስቴር አንድ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት አገደ

By Alemayehu Geremew

September 08, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር የዓለም አቀፍና የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት መመሪያን መሰረት አድርጎ ስኩል ኦፍ ኔሽን ትምህርት ቤት ላይ እገዳ መጣሉን አስታውቋል፡፡

አዲሱ የትምህርት ዘመን ከመጀመሩ በፊት በትምህርት ክፍያ ጭማሪ ዙሪያ በተደጋጋሚ ከወላጆች ቅሬታ በመቅረቡ የትምህርት ሚኒስቴር የዘርፍ አመራሮችና የባለሙያዎች ቡድን ትምህርት ቤቱንና የወላጅ ኮሚቴውን በማወያየት ከስምምነት ላይ እንዲደርሱ በተደጋጋሚ ጊዜ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል ነው የተባለው፡፡

ቢሆንም በተደረጉት ውይይቶች ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻሉ ትምህርት ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሰረት ከወላጅ ኮሚቴ ጋር ፈጥኖ በመነጋገር ምንም አይነት የትምህርት ስራ እንዳይሰራ ታግዷል መባሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡