Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በህወሓት የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የድጋፍ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በአሸባሪው ህወሓት ቡድን የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የክልሉ ትምህርት ቢሮ የድጋፍ ጥሪ አቀረበ፡፡

በሽብር ቡድኑ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ በመገንባትና የትምህርት ግብዓቶችን ለማሟላት በክልሉ መንግስት ሰፊ ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ይሁን እንጂ ጉዳቱ መጠነ ሰፊ በመሆኑ ባለድርሻ አካላት የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የበኩላቸውን እንዲወጡ የክልሉ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ይልቃል ከፍያለ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በክልሉ የበርካታ ህፃናት ቤተሰቦች በአሸባሪው ቡድን መፈናቀላቸው እና ሃብት ንብረታቸው መዘረፉ ተነግሯል፡፡

በዚህም የተማሪዎችን የትምህርት ግብዓት ለማሟላት እና የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ባለሃብቶች፣ አጋር ድርጅቶች፣ በሃገር ውስም ሆነ በውጭ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች እና ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረቡን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.