የሀገር ውስጥ ዜና

ጀግንነት የታጋይነት፣ የጽናትና የአሸናፊነት ውጤት ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

By Meseret Awoke

September 09, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ጀግንነት የታጋይነት፣ የጽናትና የአሸናፊነት ውጤት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ”ጀግንነት መልከ ብዙ ነው” ብለዋል፡፡

በዚህም የጦር፣ የግብርና ፣ የሳይንስ፣ የንግድ፣ የዕውቀት፣ የኪነ ጥበብ፣ የመንግሥት ሥራ፣ የአገልግሎት ሰጪ፣ ወዘተ ጀግኖች መኖራቸውን ገልጸዋል።

አንዱ ጀግንነት ያለ ሌላው አይኖርም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ሀገር በራሷ ቆማ፣ ራሷን ችላ፣ የራሷን ዕድል እንድትወስን ሁሉም ዓይነት ጀግኖች ያስፈልጓታል ብለዋል።

አክለውም ሀገር የምትጎዳው ጀግኖች በጎደሉበት መስክ መሆኑን አንስተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!