የሀገር ውስጥ ዜና

ግጭትን ለማስቆም የህብረተሰቡን የመፍትሔ ሃሳቦች ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ

By Meseret Awoke

September 09, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ግጭትን ለማስቆም ህብረተሰቡ የሚያነሳቸው የመፍትሔ ሃሳቦች ከውይይት ባለፈ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተመለከተ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ግጭትን መከላከልና እርቀ ሰላም ግንባታ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች እንዳሉት÷ ግጭት በአግባቡ ካልተያዘና ካልተፈታ ከመብረድ ይልቅ እየተባባሰ የመምጣት እድሉ ሰፊ ነው፡፡

በክልሉ መተከል ዞን ለዓመታት የተከሰቱትን ግጭቶች የጠቀሱት ተሳታፊው÷ ችግሩ እንዲፈታ የተካሄዱ የእርቀ ሠላም መድረኮችን የሚመሩ ግለሰቦች ሰላምን ከማውረድ ይልቅ የግል ጥቅማቸውን እንደሚያስቀድሙ ተናግረዋል፡፡

በመተከል እርቀ ሰላም ከተካሄደባቸው ቦታዎች መካከል በአብዛኞቹ ግጭት ዳግም የተቀሰቀሰበት ሁኔታ መኖሩንም ገልጸዋል፡፡

ግጭት እንዲቆም በተደጋጋሚ ህዝባዊ የውይይት መድረኮች መካሄዳቸውን አስታውሰው÷ በመድረኮቹ በህብረተሰቡ የተነሱ የመፍትሄ ሃሳቦች ከመድረክ ፍጆታ ባለፈ ተግባራዊ መደረግ አለባቸው” ብለዋል፡፡

በግጭት አፈታት የህብረተሰቡን ባህላዊ እሴቶች በሚገባ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልም ነው የጠቆሙት፡፡

አመራሮች በየመድረኩ ለህዝብ የሚገቡትን ቃል በቁርጠኝነት መፈጸም እንዳለባቸው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!