የሀገር ውስጥ ዜና

በሲዳማ ክልል ዋጋ የጨመሩና ምርት ያከማቹ ከ1ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

By Feven Bishaw

September 10, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል የዘመን መለወጫ በዓል ገበያን በመጠቀም ተገቢ ያልሆነ ዋጋ የጨመሩና ምርት አላግባብ ያከማቹ ከ1 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ወጤ ቶሼ ለኢዜአ እንደገለጹት ከህልውና ዘመቻ ጋር በማያያዝ በንግድ ስርዓቱ ላይ ተገቢ ያልሆነ ተግባር እንዳይፈጸም ግብረ ሀይል ተቋቁሞ እየተሰራ ነው። ግብረ ሀይሉ ሀዋሳን ጨምሮ በክልሉ በሚገኙ ከተሞች ከ5 ሺህ የሚበልጡ የንግድ ተቋማት ላይ ክትትል ማድረጉን ተናግረዋል።