የአፍሪካ ሕብረት ጊኒን ከአባልነት አገደ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሕብረት የፖለቲካ ጉዳዮች የሰላምና ደኅንነት መምሪያ በሃገሪቱ የተካሄደውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ ጊኒን ከዓባልነት ማገዱን አስታውቋል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት የጊኒው ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ በኮሎኔል ማማዲ ዱምቡያ በሚመራው የወታደሮች ቡድን መፈንቅለ መንግሥት የተደረገባቸው መሆኑን ተከትሎ ነው ሕብረቱ ጊኒን ከአባልነት ያገደው፡፡
መፈንቅለ መንግስቱን የጊኒ የተለያዩ ግዛቶች አስተዳዳሪዎች፣ የአፍሪካ ሕብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና አሜሪካ በጽኑ ማውገዛቸው ተገልጿል፡፡
በዚህም ሕብረቱ ጊኒን ከአባልነት ያገደ ሲሆን÷ የግዛት አስተዳደሪዎች ወደ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ለመመለስ ከአገዛዙ ጋር ሊወያዩ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
ምንጭ÷ ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!