የሀገር ውስጥ ዜና

የተለያዩ ሚኒስትሮች ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Feven Bishaw

September 10, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሚኒስትሮች ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ያለፈው 2013 ዓ.ም እንደ ሀገር ህልውናችንን የተፈታተኑ እንቅፋቶች የበዙበት የኛን እጣፋንታ ለመወሰን የውጪ እጆች የረዘሙበት አመት ሆኖ እያለፈ ይገኛል፤ ነገር ግን የዚህ አይነት ፈተናዎች ለኢትዮጵያ አጋጥመዋት የማያውቁና ለታሪኳ አዲስ የሆኑ አይደሉም ብለዋል፡፡