የሀገር ውስጥ ዜና

በጭና በአሸባሪው ህወሓት ለተጨፈጨፉ ንጹሃን የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

By Feven Bishaw

September 10, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በማይጠብሪ ግንባር በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ “ጭና” የገጠር ቀበሌ በአሸባሪው ህወሓት ለተጨፈጨፉ ንጹሃን መታሰቢያነት የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዓት በደባርቅ ከተማ ተካሄደ፡፡

በሻማ ማብራት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሰለሞን ተዘራን ጨምሮ የከተማዋ ወጣቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መገኘታቸውን ከሰሜን ጎንደር ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡