የሀገር ውስጥ ዜና

እድሳታቸው የተጠናቀቁ አራት መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላለፉ

By Feven Bishaw

September 10, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስተባባሪነት በአዲስ አበባ የ17 አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶችን ለማደስ ቃል መግባቱ ይታወሳል፡፡

በዛሬው እለትም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራርና ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም የጉለሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች በተገኙበት እድሳታቸው የተጠናቀቁ አራት መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል፡፡