የሀገር ውስጥ ዜና

ለህልውና ዘመቻው ስኬታማነት ክፍተትን የለየ የደጀንነት ተግባር ወሳኝ ነው

By Meseret Awoke

September 12, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ለህልውና ዘመቻው ስኬታማነት ክፍተትን የለየ የደጀንነት ተግባር ወሳኝ ነው የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ ዶክተር ኢንጅነር ከማል መሀመድ ገልጹ።

ለህልውና ዘመቻው አስተዋፅኦ እያበረከተ ላለው ኮምቦልቻ ከተማ ጠቅላላ ሆስፒታል በከተማው ውስጥ የሚገኙ ሰፖርት ቤቶችን በማስተባበር ብላክ ስታር ካራቴ ስፖርት ቤት ከ5መቶ ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው አልባሳት ድጋፍ አድርገዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ኢንጂነር ከማል መሀመድ በድጋፍ አሰጣጥ ስነ ስረዓቱ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት÷ ክፍትን የለየ ድጋፍ ለህልውና ዘመቻው ስኬታማነት ድርሻው ትልቅ ነው።

ስፖርት ቤቶቹ የሰውን አዕምሮ እና ሰውነት እንዲጎለብት ከማድረግ በተጨማሪ ለሠራዊቱ ደጀን በመሆን ያደረጉት ትልቅ ነገር እንደሆነ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ የማህበረሰቡ ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ዶ/ር ኢንጅነር ከማል መሐመድ ተናግረዋል።

የተደረገው የአልባሳት ድጋፍ በህክምና ላይ ለሚገኙ የመከላከያ መሠረታዊ አባላት አገልግሎት የሚውል ነው።

በእሸቱ ወ/ሚካኤል

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን