Fana: At a Speed of Life!

አፋር ክልል ለ40 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል መንግስት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ40 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።

የክልሉ ጠቅላይ አቃህግ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሳ ያሲን እንደገለጹት÷ በይቅርታ ቦርድ ተመርምሮ መስፈርቱን አሟልተው ለተገኙ ታራሚዎች ይቅርታው ተደርጓል።

“ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል በፈፀሙት ወንጀል የተፀፀቱ፣ አብዛኛውን የእስር ጊዜያቸውን የጨረሱ፣ በዕድሜያቸው የገፉና የጤና ዕክል ያጋጠማቸው ይገኙበታል” ብለዋል።

በሙስና፣በሀገር ክህደትና ተያያዥ ከፍተኛ ወንጀሎች የፍርድ ውሳኔ የተሰጣቸው ታራሚዎች በይቅርታው አለመካተታቸውን ገልጸዋል።

የይቅርታው ተጠቃሚ የሆኑት 40 ታራሚዎች ከያሉቧቸው ማረሚያ ቤቶች ከመስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንዲወጡ መወሰኑን አቶ ሙሳ ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎችም ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ያሳዩትን መልካም ስነ-ምግባር በማስቀጠል የበደሉትን ህብረተሰብ በልማት እንዲክሱ አስገንዝበዋል።

ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል በአውሲ-ረሱ ማረሚያ ቤት ታራሚ የነበሩ አቶ መሀመድ አሊ መንግስት የሰጣቸውን ይቅርታ ተጠቅመው በቀሪ ህይወታቸው ህግን አክብረው በመንቀሳቀስ ማህበረሰቡን ለመካስ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.