የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ በቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

By Tibebu Kebede

February 04, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክትም ለኬንያውያን መጽናናትን ተመኝተዋል።

ከኬንያ ነጻነት በኋላ ሁለተኛው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት በመሆን ለ24 ዓመታት ሀገሪቱን የመሩት ዳንኤል አራፕ ሞይ በ95 ዓመታችው ማረፋቸው ተነግሯል።