የሀገር ውስጥ ዜና

በአብዬ ለተሰማራው የ25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አመራሮችና አባላት እውቅና ተሰጠ

By Feven Bishaw

September 12, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በአብዬ የተሰማራው የ25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አመራሮችና አባላት አስተማማኝ ሰላምን በማስፈን ላበረከቱት አስተዋፅዖ በተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር የእውቅና ሰርተፍኬትና የሜዳልያ ሽልማት ተሰጣቸው፡፡

የዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዥ ሜጀር ጄነራል ከፍያለው አምዴ ‘ በከፍተኛ ወታደራዊ ዲሲፕሊን ሙያዊ ስነ ምግባር እንዲሁም በዩኒስፋ የግዳጅ አፈፃፀም መመሪያዎችና ደንቦች እየተመራችሁ ሁሉንም አይነት ግዳጅ ለዓለም ምሳሌ ሊሆን በሚችል ደረጃ በመፈፀማችሁ የሻለቃችሁን እንዲሁም የአገራችሁን ስምና ክብር ከፍ ባለ ደረጃ አስጠርታችኋልና ልትኮሩ ይገባችኋል ብለዋል፡፡