የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ሰመራ ገቡ

By Feven Bishaw

September 13, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ፣የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ እንዲሁም ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አፋር ክልል ሰመራ ገብተዋል፡፡

የደቡብ ክልል አሸባሪው የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ በማለም ነው ዛሬ በምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የተመራ ልኡክ ወደ ሰመራ ያቀናው ።