Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ከ4 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ መከናወኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ክልል ከ4 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ መከናወኑ ተገለፀ፡፡

የ2012 ዓም ክልል አቀፍ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ ፕሮግራም በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ እየተካሄደ ነው።

በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የግብርና ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ተፈራ ታደሰ እንደገለፁት ÷ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለውን የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ ስኬታ በሆነ መንገድ ለማስፈፀም በተካሄደ ጥረት አበረታች ስራዎች ማከናወን ተችሏል።

የዘንድሮውን የተፋሰስ ልማት ስራ ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት መሰራት እንዳለበትም ጠቁመዋል።

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ ተወካይ የሆኑት አቶ መለሰ መና በበኩላቸው፥  ከዚህ በፊት የተከናወኑ ስራዎች በርካታ ለውጦች መፍጠራቸውን  ተናግረዋል።

የተቀናጀ  የተፋሰስ ልማት ስራ በርካታ በረከቶች ያሉት በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አንስተዋል።

ባዛሬው ዕለት በኦፋ ወረዳ የተጀመረው የተቀናጀ  የተፋሰስ ተግባር ለአንድ ወር በክልል አቀፍ ደረጃ የሚከናወን ይሆናል።

በዚህም 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ህዝብ የሚሳተፍበት 404 ሺህ ሔክታር መሬት ይሸፍናል ተብሏል።

በአጠቃላይ አንድ ቢሊየን ችግኞች የተከሉ   ሲሆን በከፍተኛ ጥንቃቄ መተግበር እንደሚገባ ተመላክቷል።

ከመድረኩ ጎንለጎን የተለያዩ  የመስኖ ልማት ስራዎች እና የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች ጉብኝት ተደርጓል።

በብርሃኑ በጋሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.