Fana: At a Speed of Life!

በኬንያ በመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በተፈጠረ መገፋፋት የ13 ተማሪዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)በኬንያ በሚገኝ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በተፈጠረ መገፋፋት በትንሹ የ13  ተማሪዎቸ ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

በኬንያ ምዕራባዊ ክፍል በሚገኘው በካካሜጋ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በተፈጠረው አደጋ በ39 ተማሪዎች ላይ  ከባድ የአካል ጉዳት እንዳጋጠማቸው  ነው የተነገው፡፡

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ሆስፒታል ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የካካሜጋ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ይህ አደጋ የተከሰተው ተማሪዎች ወደ  ቤት መሄድ ሲጀመሩ በተፈጠረ ድንጋጤ ሲሆን የዚህ ድንጋጤ  ምክንያት አለመታወቁ  ነው የተነገረው ፡፡

የተፈጠረው ነገር በትክክል ለማወቅ ምርመራ እየደረገ መሆኑን የከተማዋ ፓሊስ ገልጿል።

የኬንያ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራኢላ ኦዲንጋ በአደጋው የተሰማቸውን ሀዘን በትዊተር ገፃቸው ገልጸዋል ፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.