የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ በፖሊስ ኮሌጅ ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች ተመረቁ

By Meseret Awoke

September 14, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ በፖሊስ ኮሌጅ ስልጠና የወሰዱ 259 ወጣቶች ተመረቁ።

ከተመራቂዎቹ መካከል 32ቱ የፖሊስ አባላት ሲሆኑ÷ ቀሪዎቹ የማርሻል አርት ስፖርተኞችና በጎ ፍቃደኛ የሰላም አስከባሪዎች ናቸው።

ሰልጣኞቹ ወደ ስራ ሲሰማሩ የአካባቢያቸውንና የከተማዋን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸውየተገለጸ ሲሆን÷ በቀጣይም ወጣቶችን ለማሰልጠን የምልመላ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተጠቅሷል።

ስልጠናው “እኔ የከተማዬ የሰላም ዘብ ነኝ” በሚል መርህ መከናወኑም ተገልጿል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማዋ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!