የሀገር ውስጥ ዜና

ወረዳው በአሸባሪው ትህነግ ጉዳት የደረሰባቸውን ተማሪዎች በነፃ ተቀብሎ ለማስተማር ወሰነ

By Meseret Awoke

September 14, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትህነግ አሸባሪ ሃይል በፈጸመው ወረራና ጅምላ ጭፍጨፋ የጦርነቱ ሰለባ የሆኑ ተማሪዎችን በምስራቅ ጎጃም ዞን የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ አስተዳደር ለአንድ ዓመት በነፃ ለማስተማር ወረዳው ወስኗል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተመስገን ዘውዴ ለፋና እንደገለጹት÷ አሸባሪው ቡድን በሰው ልጅ ህይወት ላይ ከፈጸመው አሰቃቂ እልቂት፣ በተቋማት ላይ ያደረሰው ውድመት አሳዛኝ መሆኑን ነው ብለዋል።

በመሆኑም በወረዳው በሚገኙት 57 ትምህርት ቤቶች ውስጥ የችግሩ ሰለባ የሆኑ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለአንድ ዓመት ለማስተማር የወረዳው ምክር ቤት ወስኗል።

የወረዳው አስተዳደር ተማሪዎችን ተቀብሎ በነፃ ለማስተማር የወሰነው በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎችን እንደሆነም ተጠቅሷል።

በተመስገን ዘውዴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!