የኢሬቻን በዓል ያለ ምንም እንከን ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል – የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሞ ህዝብ የአንድነትና የሰላም ተምሳሌት የሆነውን የኢሬቻን በዓል ያለ ምንም እንከን ለማክበር ዝግጅት መደረጉን የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት አስታወቀ።
ህብረቱ መስከረም 22 እና 23/2014 ዓ.ም የሚከበረውን የዘንድሮውን ኢሬቻ በዓል በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የአባገዳዎች ህብረት ምክር ቤት ሰብሳቢ አባገዳ ጂሎ ማኖ እንደገለጹት፥ በኢሬቻ ውስጥ ፖለቲካ የለም፣ ሰላምና ምስጋና ነው።
“ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ የአንድነትና የሰላም ተምሳሌት ነው፥በዓሉን ያለምንም እንከን ለማክበር ተዘጋጅተናል ነው” ያሉት።
ዕለቱ የኦሮሞ ህዝብ በአንድነት ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት በመሆኑ በዓሉ ያለምንም ችግር በሰላም እንዲከበር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም አስገንዝበዋል።
የህብረቱ ፀሐፊና የቱለማ አባገዳ ጎበና ሆላ በበኩላቸው፥ በዓሉ የኦሮሞ ህዝብ ባህልና ትውፊቱን፣ ማንነቱ፣ የሰላምና የአንድነት ተምሳሌት መሆኑን የሚያሳይበት ነው ብለዋል።
የበዓሉ ታዳሚ ህዝብ በዓሉን ሲያከብር ከኮሮና ወረርሽኝ ራሱን በመጠበቅ መሆን እንደሚገባውም አሳስበዋል።
በተለይ በዓሉን የፖለቲካ ትርፍ ይገኝበታል ብሎ የሚያስቡ ሃይሎች መጠቀሚያ እንዳያደርጉት የኦሮሞ ቄሮዎች፣ ቀሬዎች እና ፎሌዎች በየደረጃው ከሚገኙ የፀጥታ ሃይሎች ጋር በትብብር መስራት እንዳለባቸውም አመልክተዋል።
ኦሮሚያን ጨምሮ የሀገሪቱ ክልሎችና ከውጭ የሚመጡ እንግዶች በሰላም በዓሉን ታድመው ወደ መጡበት እስኪመለሱ ድረስ የመንግስት የፀጥታ ሃይሎችና መላው ህብረተሰብ ትብብር እንዲያደርጉም ህብረቱ መጠየቁን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
6
Engagements
–
Distribution Score
Boost Post
6