የሀገር ውስጥ ዜና

አፍሪካውያን በአንድነት መቆም አለብን – ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል

By Meseret Awoke

September 15, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)አፍሪካውያን በአንድነት በመቆም በአለም ላይ ያለንን ድርሻና ጥቅም አስጠብቀን መቆየት አለብን ሲሉ የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቀናት በፊት በትዊተር ገጻቸው አስፍረውት የነበረውን መልዕክት በመጋራት ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሰፈሩት መልዕክትም ‘’የእኛ የአፍሪካውያን ትብብር ለሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ነው’’ ብለዋል፡፡

በዚህም ፕሬዚዳንት ማኪ አህጉራችን ብዙ ኢኮኖሚያዊ ዕድሎች አሏት ያሉ ሲሆን÷ በትብብር ይህ እንዲሳካ ማድረግ አለብን ሲሉ በትዊተር መልዕክታቸውን አስፍረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!