ጤና

አሳሳቢው ኮቪድ-19 የብዙሃንን ህይዎት እየቀጠፈ ነው

By Meseret Awoke

September 15, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ በሁለት ቀናት ውስጥ በኮቪድ-19 ህይዎታቸው ያለፈ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡

የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ዝርያ የሆነው ዴልታ መከሰቱን ተከትሎ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ወደዕለት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን መግለጹ ይታወሳል፡፡

በዚህም በቫይረሱ ተይዘው በጽኑ ህክምና ክትትል የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥርም በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ይህን ተከትሎም በቫይረሱ ሳቢያ በሁለት ቀናት ብቻ የ72 ሰዎች ህይዎት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!