የማላዊ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ሰረዘ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የማላዊ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባለፈው ዓመት የተካሄደውን አከራካሪ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ሰረዘ፡፡
በግንቦት ወር በተካሄደው ምርጫ ፔተር ሙታሪካ 38 በመቶው ድምፅ በማግኘት የማላዊ ፕሬዚዳንት መሆናቸው ይፋ ሆኖ የነበረ ሲሆን ÷በወቅቱ ላዛሩስ ቻክዌራ 35 በመቶውን ድምፅ እንዲሁም የሀገሪቱ የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት 20 በመቶ ድምፅ በማግኘት ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ነበር።
ይህንን ተከትሎ በውጤቱ ያልተደሱ ሁለቱ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች ፊርማ በማሰባሰብ በምርጫ ሂደት ላይ ህገ ወጥ ተግባራት ተፈፅመዋል ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።
ማሊያዊያንም የምርጫው ውጤት ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ጄን አንሳ ከሃላፊነት እንዲለቁ ተቃውሞ ሲያሰሙ ቆይተዋል።
የሀገሪቱ ፍርድ ቤትም ባሳለፈው ውሳኔ በ150 ቀናት ውስጥ አዲስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንዲካሄድ ትእዛዝ አስተላልፏል ፡፡
ውሳኔውን ለማስተላለፍ ለ10 ሰዓታት የዘለቀ ጊዜ መውሰዱ ነው የታወቀው፡፡
ፍርድ ቤቱ አዲሱ ምርጫ የዜጎችን የሰብዓዊ መብት በማክበር እንዲከናወን ተጨማሪ ትእዛዝ ማስተላለፉ ታውቋል፡፡
በአውሮፓውያኑ 2017 የኬንያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ከተሰረዘ በኋላ ማላዊ ተመሳሳይ ውሳኔ በማሳለፍ ሁለተኛዋ ከሰሃራ በታች የምትገኝ ሀገር ሆናለች ፡፡
ምንጭ፡- አልጀዚራ