የሀገር ውስጥ ዜና

ትምህርት ሚኒስቴር በአማራ ክልል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለማቋቋም የ100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

September 16, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት በአማራ ክልል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለማቋቋም የትምህርት ሚኒስቴር 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

አሸባሪው እና ወራሪው የትህነግ ቡድን በአማራ ክልል በፈጸመው ወረራ ከ2 ሺህ 950 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኅላፊ ዶክተር ይልቃል ከፋለ ገልጸዋል።

በጉዳቱም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዲርቁ ተገደዋል ብለዋል፡፡

እብሪት የወለደው ድንቁርና ሕጻናት በወርኃ መስከረም እንዳይማሩ አድርጓል ያሉት የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ÷ ችግሩን የከፋ የሚያደርገው በጦርነቱ ወላጆቻቸውን ያጡ እና የተጎዱ ሕጻናት መኖራቸው ነው ብለዋል፡፡

ችግሩን ከስር ከስር መፍታት እና ማቃለል አሰፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል ያሉት ሚኒስትሩ በመደበኛ ከሚደረገው ድጋፍ በተጨማሪ ትምህርት ቤቶቹን ለመጠገን 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደርጓል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!