የሀገር ውስጥ ዜና

የሚዲያ ባለሙያዎች ጉብኝት ለሰራዊቱ የሞራል ስንቅ ነው

By Meseret Awoke

September 16, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ስራ አስፈፃሚዎች ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች እና በህልውና ዘመቻ እየተሳተፉ የሚገኙ የሰራዊት አባላትን ግንባር ድረስ ተገኝተው ጎብኝተዋል።

ቡድኑ በደቡብ ጎንደር ዞን እና ሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ በህወሓት የሽብር ቡድኑ የደረሱ ውድመቶችን እና ሰብዓዊ ጥፋቶችን ተመልክቷል።

በተጨማሪም በጋሸና ግንባር በመገኘት የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይል እና ሚሊሻ እንዲሁም ወጣቶችን አበረታተዋል።

በመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ የመገናኛ ብዙሃን እና የኮምኒኬሽን ባለሙያወች ጉብኝት ሰራዊቱ እያደረገ ለሚገኘው ሀገር የማዳን ዘመቻ ትልቅ የሞራል ስንቅ እና ተነሳሽነትን የሚፈጥር ነው ብለዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ እና ህዝቡ በደጀንነት ለሚያደርገውን ድጋፍ አመስግነው÷ በአጭር ጊዜ የሽብር ቡድኑ እንደሚደመሰስ አንስተዋል።

በምንይችል አዘዘው

ተጨማሪ ምስል ከኢዜአ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!