ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስልጣን አገዱ

By Meseret Awoke

September 16, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ የጠቅላይ ሚኒስትር ሞሀመድ ሁሴን ሮብልን ባለስልጣናትን የመሾም እና የመሻር ስልጣን አግጃለሁ ብለዋል፡፡

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የሆኑት አብዱላሂ ሞሃመድ(ፋርማጆ) የሃገሪቱንጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን አግደዋል፡፡

የእገዳ ውሳኔውም የደህንነት መስሪያ ቤት ሰራተኛ ኢክራም ታህሊል ፋራህ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት መሰወርን ተከትሎ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

በሶማሊያ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ያለው መከፋፈል መጪዎቹ ምርጫዎች ላይ ስጋት እንደሚጭር እየተዘገበ ነው።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!