አቶ ወርቁ አይተነው በደሴ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው በደሴ መጠለያ ጣቢያዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች እየተደረገ ያለውን ድጋፍ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ለተፈናቃዮች እየተደረገ ያለውን ድጋፍ ከተመለከቱ በኋላ÷ በሚያስፈልጋቸው ተጨማሪ ድጋፍ ላይ ከተፈናቃዮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ ለእስካሁኑ ድጋፍ የደሴ ከተማን ህዝብ አመስግነው÷ አሁን ላይ ድጋፉ እየቀነሰ በመሆኑ ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ሁኔታ እንዲመቻች ጠይቀዋል፡፡
ለልመና እጃችንን ከምንዘረጋ ጠላትን በጋራ መፋለም አማራጭ የሌለው መፍትሄ በመሆኑ÷ ተደራጅተን አሸባሪውን ህውሓት መታገል እንፈልጋለንም ብለዋል፡፡
እናት በየመንገዱ እየወለደች ነው ጥለን የመጣነው ያሉት ተፈናቃዮቹ÷ ህውሓትን ሰርጎ ከገባበት አካባቢ ለማስወጣት እና ወደ መደበኛ ኑሯችን ለመመለስ ከፊት ሆነነን መፋለም እንፈልጋለን ነው ያሉት፡፡
ከሞት የተረፉት ቤተሰቦቻችን በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ በመሆናቸው በተደራጀ አግባብ ጠላትን መፋለም ይገባል ብለዋል፡፡
ወደ አካባቢያችሁ በቅርቡ ትመለሳላችሁ ያሉት አቶ ወርቁ÷ ለህልውና ዘመቻው የሚደረገው ድጋፍም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡
ተደራጅቶ መታገሉ ትክክለኛ መፍትሄ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ወርቁ የጎደለውን እና ለእናንተ የሚያስፈልገውን ሁሉ እናሟላለን ብለዋል፡፡
በሀብታሙ ተክለ ሥላሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!