የሀገር ውስጥ ዜና

በሀረሪ ክልል “የነጩ ፖስት ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄ ተጀመረ

By Feven Bishaw

September 17, 2021

አዲስ አበባ ፣መስከረም 7፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል “የነጩ ፖስት ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በዛሬው እለት ተካሂዷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ዘመቻውን ባስጀመሩበት ወቅት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው አሸባሪው የህወሓት ቡድን በተለይም በአሁኑ ወቅት የአማራ እና አፋር ክልል ህዝቦች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።