የሀገር ውስጥ ዜና

የጤና ሚኒስቴር ከፖሊሽ ሴንተር ፎር ኢንተርናሽናል ኤይድ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

By Feven Bishaw

September 17, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር የድንገተኛ አደጋ እና የፅኑ ህክምና አገልግሎት ለማሻሻል ከፖሊሽ ሴንተር ፎር ኢንተርናሽናል ኤይድ ጋር ለሶስት አመት የሚቆይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱ ለአንቡላንስና ድንገተኛ አደጋ ህክምና የሚውሉ ግብአቶችን ማቅረብ፣ ለድንገተኛ ህክምናና ፓራሜዲክ ባለሞያዎች ስልጠና፣ የቅድመ ጤና ተቋም አገልግሎትን ለማሳለጥ የጥሪ እና ስምሪት ማዕከል ማጠናከር፣ ለትራፊክ እና በጅምላ ለሚደርሱ አደጋዎች ምላሽ አሰጣጥን የሚያሻሽሉ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ያካትታል ተብሏል፡፡