የሀገር ውስጥ ዜና

14 ሺህ የክላሽ ጥይት ተያዘ

By Tibebu Kebede

September 18, 2021

 

አዲስ አበባ ፣መስከረም 7፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መነሻውን ደሴ በማድረግ ባህርዳር ከተማ ላይ 14 ሺህ የክላሽ ጥይት በቁጥጥር ዋለ።

በዛሬው ዕለት ከምሽቱ 3:30 ሰዓት መነሻውን ደሴ በማድረግ በመካነሰላም መርጦ ለማሪያም ሞጣ ባ/ዳር መስመር የታርጋ ቁጥር ኮድ3 አአ 59582 የሆነ ሲንግል ካፕ መኪና ሻግ በማሰራት 14 ሺህ የክላሽ ጥይት በደብቅ ሲጓጓዝ ባ/ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ሁሴን አህመድ እና መሃመድ አደም ከተባሉ ተጠርጣሪዎች ጋር እጅ ከፍንጅ ከክልሉ ፓሊስ አባላት ጋር በጋራ በመሆን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከመነሻዉ ደሴ ጀምሮ እሰከ መዳረሻዉ ባ/ህርዳር ከተማ ሚስጥራዊ ክትትል በማድረግ ለክልሉ ፖሊስ ጥቆማና መረጃ በመስጠት ተጠርጣሪዎች እንዲያዙና ህገወጥ የግንኙነት መረቡ እንዲበጣጠስ ያደረገዉ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ነዉ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!