ዓለምአቀፋዊ ዜና

በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ በሁለት ወራት ውስጥ ከ500 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል- ተመድ

By Tibebu Kebede

February 04, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2012(ኤፍቢሲ) በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ባለው ጦርነት በሁለት ወራት ውስጥ ከ 500 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።

ድርጅቱ ባወጣው ሪፓርት በሩሲያ የሚደገፈው የመንግስት ጦር የአማፂያኑን የመጨረሻ ይዞታ ለመቆጣጠር በሚያርገው ጥረት በሁለት ወራት ውስጥ 520 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገልጿል።

ከተፈናቀሉ ዜጎች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች እና ህፃናት መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አድርጓል።

ከሶስት ሚሊየን የሚበልጡ ሰዎች ለአደጋ መጋለጣቸውን ነው ድርጅቱ ያስታወቀው።

ግማሾቹ በመንግስት ስር ቁጥጥር ስር ወደ ሚገኙ ኢድሊብ እና አካባቢው እንደተዘዋወሩ  የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቃል አቀባይ ስዋንሰን አስታውቀዋል ፡፡

የሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ወቅታዊ ሁኔታ የመድሃኒት እጥረት ፣ መፈናቀል እና ከንጽህና ችግር ጋር ተያይዞ ለሚከሰቱ ነገሮች አደጋ ጋርጧል ሲሉ የአለም የጤና ድርጅት የክልሎች አስቸኳይ ዳይሬክተር ሪክ ብሬናን ገልጸዋል፡፡

ቀጠናው በከባድ ሁኔታ በሰብአዊ ቀውስ እየተፈተነ  እንደሚገኝም  ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ