የሀገር ውስጥ ዜና

በአሸባሪው ህወሓት ቡድን “ቁርአንና ኪታቦቻችን ዝናብ ላይ ተጥለዋል” – የኮምቤ መስጅድ ኢማም

By Tibebu Kebede

September 18, 2021

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህወሀት ቡድን “ቁርአንና ኪታቦቻችን ዝናብ ላይ ተጥለዋል ምንጣፎቻችን ተዘርፈዋል ሲሉ ሸህ አህመድ ሲራጅ የኮምቤ መስጅድ ኢማም ተናገሩ፡፡

በሰሜን ወሎ በሚሌ ወንዝ አድርጎ ወደ ወረባቦ ወረዳ ገብቶ የነበረው የአሸባሪው ህወሀት ቡድን ከወረዳው ተጠራርጎ በወጣበት ሰአት ንፁሀንን ገድሎ ሀብትና ንብረቶችን ዘርፎ ይዞ መሄድ ያልቻላቸውን አውድሟል።

ይህ የጥፋት ሀይል ንብረቶችን ሲዘርፍና ሲያወድም የግለሰብ ንብረቶችንና የመንግሰት ንብረቶችን ብቻ ሳይሆን የሀይማኖት ተቋማትን ጭምር በመሆኑ ከ018 ቀበሌ ኮንቤ መስጅድ ያገኘውን የመስገጃ ምንጣፍ መዝረፋቸውን ሸህ አህመድ ሲራጅ ተናግረዋል።

እንደ ሸህ አህመድ ገለፃ እነዚህ ሰዎች ፈጣሪን የማያውቁ መሆናቸውን ከተግባራቸው አይተናል በመስጅዱ የነበሩ ቁርአንና ኪታቦች እውጭ ዝናብ ላይ ጥለዋቸው እነሱ መስጂድ ውስጥ እየጨፈሩ ጥይት እየተኮሱ ቆርቆሮውንና ግድግዳውን መተውታል።

ለመስገጃነት የተገዙልን ምንጣፎች ጨርሰው ተወስደዋል ማለታቸውን ከወረባቡ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!