የሀገር ውስጥ ዜና

12 ቋንቋዎችን አቀላጥፎ የሚናገረው የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪ

By Tibebu Kebede

September 18, 2021

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩኒቭርስቲ ቆይታው ተጨማሪ 6 ቋንቋዎችን አቀላጥፎ በመናገሩ በዩንቨርስቲው እንዲቀጠር እና 2ተኛ ዲግሪ እንዲማር እድል ተሰጥቶታል፡፡

አደም ከድር በሶሾሎጂ የተመረቀ ሲሆን አፋን ኦሮሞ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ፣ አረብኛ፣ ሱዳንኛ፣ ሰልጤኛ፣ ሀዲየኛ ና ሌሎችንም አቀላጥፎ ይናገራል ።

የአፍ መፍቻ ቋንቋው ሲዳምኛ ሲሆን ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጣ 6 ቋንቋዎችን ይናገር ነበር። አደም በዩኒቭርስቲ ቆይታው ይህንን የቋንቋ ችሎታውን ወደ 12 ማሳደግ ችሏል።

ዩኒቨርስቲውም አደም በነበረበት የማህበረሰብ ሳይንስና ሂዩማኒቲ ኮሌጅ ላደረገው የነቃ ተሳትፎ እና ለልዩ ችሎታው በዩንቨርስቲው እንዲቀጠር እና 2ተኛ ዲግሪ ትምህርቱን እንዲማር እድል ሰጥቶታል።

በቅድስት ዘዉዱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!