የሀገር ውስጥ ዜና

በሸባሪው ቡድን የጤና አገልግሎት በተቋረጠበት ጤና ኬላ ባለሙያዎች የህክምና ድጋፍ እያደረጉ ነው

By Tibebu Kebede

September 18, 2021

 

አዲስ አበባ ፣መስከረም 8፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከግልና ከመንግስት የጤና ተቋማት የተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ድሬ ሮቃ ቀበሌ በመገኘት የህክምና ድጋፍ አደረጉ፡፡

ከአሸባሪው የህወሓት ቡድን በአካባቢዉ ያለዉን የኮምቦልቲ ጤና ኬላን ከጥቅም ውጪ አድርጎት በመሄዱ ህብረተሰብ ከፍተኛ ለሆነ የጤና እክል ተዳርጎም ቆይቷል።

ችግሩ እየተባባሰ እንዳሄድም የደቡብ ወሎና ደሴ ከተማ ጤና መምሪያዎች ከቦሩ ሜዳ ሆስፒታልና በደሴ ከተማ ካሉ የግል ጤና ተቋማት ጋር በመተባበር በሚቀጥሉት ሦስት ቀናቶች የሚቆይ የህክምና ድጋፍ ማድረግ ጀምረዋል።

ጥምረቱ በሚቀጥሉት ጊዜያትም በአካባቢው ያሉ የጤና ተቋማት መደበኛ አገልግሎታቸውን መስጠት እስከሚጀምሩ ድረስ ቀጣይነት ያለዉ ስራ ይሰራል ብለዋል የመምሪያዎቹ ኃላፊዎች።

የአሸባሪዉ የህወሓት ቡድን የሽብር ስራም ህፃናትን፣ ሴቶችና አቅመ ደካማ አረጋውያን ህክምና እንዳያገኙ በማድረግ ለከፋ ጉዳት ዳርጓቸዋል።

በኢሳያስ ገላው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!