የሀገር ውስጥ ዜና

የ25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ማንኛውንም ግዳጅ በብቃት መወጣት የሚችል ነው – የተመድ ቡድን

By Feven Bishaw

September 19, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአብዬ የሚገኘው የ25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ማንኛውንም ግዳጅ በብቃት መወጣት በሚያስችለው ቁመና ላይ እንደሚገኝ የተመድ የሰላም አስከባሪ ጦር በአብዬ ኢኒስፔክሽን ቡድን ማረጋገጡ ተገለፀ፡፡

የሻለቃው ዋና አዛዥ ኮሎኔል ሌንጮ ኤደኦ እንደተናገሩት ÷ ቡድኑ ይህንን ማረጋገጡ አመራርና አባላቱ ዛሬም እንደከዚህ በፊቱ የአገራቸውን ክብርና ዝና በማስጠበቅ እውነተኛ የሰላም አምባሳደር መሆናቸውን በተግባር አሳይተዋል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡