የሀገር ውስጥ ዜና

የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች ከአሜሪካ ኮንግረስ አባል ካረን ባስ ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

September 19, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ በጋራ በመሆን የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ከሆኑት ካረን ባስ ጋር ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት አዲስ አበባ የገቡት የአሜሪካ ኮንግረስ አባላቱ ካረን ባስ እና ሳራ ጃኮፕስን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር መወያየታቸው ይታወቃል።