የሀገር ውስጥ ዜና

የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል ለወሰኑ የጅማ ወጣቶች ሽኝት ተደረገ

By Tibebu Kebede

September 19, 2021

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጅማ ዞንና ከተማ ተወጣጥተው የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለቀላቀል ዝግጁ ለሆኑ ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸው፡፡

የሽኝት መርሃ ግብሩ በጅማ ዩኒቨርስቲ ስቴዲየም በተካሄደው ሲሆን፣ የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ቲጃኒ ናስር ባደረጉት ንግግር ሀገር ተነካች ብላችሁ የሀገራችሁን ሉዓላዊነት ለማስከበርና ህዝቦችሁን ከጥቃት ለመጠበቅ ላሳያችሁት ተነሳሽነት ኢትዮጵያ ታመሰግናችዋለች ብለዋል።

የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱላኪም ሙሉ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአፍሪካ መከታ መሆኑን ተናግረው ፣ የዛሬ ዘማች ወጣቶች ከሀገራችሁ አልፋችሁ የነገ የአፍሪካ ጄኔራሎች ናችሁ በማለት ወጣቶቹን ሸኝተዋል፡፡

የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ተቀላቅለው ሀገር ለማዳን እየዘመቱ ያሉ ወጣቶች እንደተናገሩት ኢትዮጵያ እኛ እያለን ነፃነቷ አይደፈርም ብለዋል።

ከዚህ ቀደምም በሁለት ዙሮች ከጅማ ከተማ እና ከጅማ ዞን የተውጣጡ ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሰራዊትን መቀላቀላቸው ይታውሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!