የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከህግሎለይ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

September 19, 2021

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከህግሎለይ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

የህግሎለይ ወረዳ እና አከባቢው ባለፉት 27 አመታት አሸባሪው የህወሃት ጁንታ በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከፈፀመባቸው የክልሉ አከባቢዎች የሚትጠቀስ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ÷ምንም አይነት የልማት ስራዎች እንዳልተከናወኑ የወረዳው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ባለፉት ሦስት አመታት በክልሉ በተፈጠረው ለውጥ ዜጎች በነፃነት መንቀሳቀስ መቻላቸውና ከልማቱም ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ገልፀዋል።

የህግሎለይ ወረዳ ለዘመናት ያልነበራት የስልክ አገልግሎት ጥያቄም መልስ ያገኘ ሲሆን ÷አሁን ላይ የቴሌኮም ታወር ተተክሎ የወረዳው ነዋሪ የስልክ ተጠቃሚ መሆን ችሏል ነው የተባለው።

የወረዳው ነዋሪዎች ያለባቸውን ሌሎች የልማት ጥያቄዎች በተለይ የመንገድ ልማት መንግስት እንዲመልስላቸው መጠየቃቸውን የሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ሙስጠፌ መሃመድ÷ የክልሉ መንግሥት የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች በተለይ የውሃ፣ የመንገድ እንደሚመልስ ገልፀው በቅርቡ ዘመናዊ የ24 ሰዓት የሶላር መብራት አገልግሎት ለህግሎለይ ወረዳ እንደታቀደ ገልፀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!